መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 27፣2012-በፎርጅድ አንድ መቶ ብር ሙዝ የገዛው ሰው ሀሰተኛ ገንዘብ የሚያመርተዉን ተጠርጣሪ እንዲያዝ አደረገ

በአዳማ ከተማ ሉጎ ክፍለ ከተማ ቢቃ ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ፖስታ ቤት ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ግንቦት 25 ቀን ከቀኑ 9 ሰዓት አንድ ተጠርጣሪ ሙዝ ለምትሸጥ ነጋዴ ሀሰተኛ መቶ ብር በመስጠት ሙዝ ይገዛል፡፡ሽያጩ ከተከናወነ በኃላ ሀሰተኛ ገንዘቡ ያጠራጠራት ነጋዴ ለፖሊስ ጥቆማ ታደርሳለች፡፡

ፖሊስ በተሰጠዉ ጥቆማ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር ያዉላል፡፡በቁጥጥር ስር የዋለዉ ተጠርጣሪ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣ ሲጠየቅ ወደ ዋና ተጠርጣሪ ጥቆማ ይሰጣል፡፡ፖሊስም የዋና ተጠርጣሪ አድራሻ ወደሆነዉ አዳማ ወረዳ አዱላላ ቀበሌ ልዩ ቦታዉ አጤ አሮሪቲ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ተከራይቶ የሚኖረዉን ዋና ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ያዉላል፡፡

ፖሊስ በዋና ተጠርጣሪ መኖሪያ ቤት ባደረገዉ ፍተሻ የሀሰተኛ ገንዘብ ማምረቻ ማሽን ከነ ሙሉ ቀለሙ የተለያዩ ባንክ ቤት የንዝብ ደብተር፣መንጃ ፍቃድ እና የተለያዩ ሰዎች ፎቶ ሊያገኝ ችሏል፡፡

በተጨማሪም 77 ሺህ 575 ብር ሐሰተኛ የብር ኖት ባለ 100 ብር 75 ሺህ፣ ባለ 50 ብር 2 ሺህ 550 ብር፣ ባለ 10 ብር ሁለት፣ ባለ 5 ብር አንድ እና 3 የሳዑዲ አረቢያ ሪያል ሊያዝ መቻሉን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኝነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *