መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 27፣2012-አማዞን ከህንዱ የቴሌኮም ካምፓኒ ብሃርቲ ኤየርቴል ፤ የ 2 ቢሊዮን ብር አክሲዮን ሊገዛ መሆኑ ተነግሯል

ምንጮች ለሬውተርስ እንደተናገሩት ግዙፉ የኦንላይን የገበያ ስፍራ የሆነው አማዞን ከሞባይል ኦፕሬተሩ ብሃርቲ ኤየርቴል ጋር የሚያደርገው ድርድር ከስምምነት ሳይደር እንዳልቀረ ነው፡፡

የአሜሪካ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም ኢኮኖሚዋ በማደግ ላይ በምትገኘው ህንድ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎት እያደረባቸው መምጣቱ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱ እንደተባለው ግቡን ከመታ አማዞን 5 በመቶ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ብሃርቲ በህንድ ከሚገኙ ሶስተኛው ትልቅ የቴሌኮም ተቋም ሲሆን ከ 300 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ተገልጿል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *