~ በፔሩ ሆስፒታሎች ለአጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ የሚሆን የኦክስጅን እጥረት አጋጥሟል።በሌላ የፔሩ መረጃ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃችው የ50 ዓመቷ እናት በሰላም መንታ ልጆችን የተገላገለች ሲሆኑ ህፃናቱ ከቫይረሱ ነፃ ናቸው።
~ ጋቪ ክትባት የተሰኘ ጥምረት ለታዳጊ ሀገራት የኮሮና ሻይረስ ክትባት መድሃኒት መግዣ የሚውል ገንዘብን ማሰባሰብ ጀምሯል።ጥምረቱ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከዓለም አቀፍ ለጋሾች እንደሚያገኝ ከወዲሁ ቃል ተገብቶለታል።
~ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ድንበራቸውን መክፈት ጀመሩ።ከኦስትሪያ፣ጀርመንና ሀንጋሪ ለሚመጡ ዜጎች ቼክ ከነገ ጀምሮ ድንበሯን ትከፍታለች።በክሮሺያና ሀንጋሪ መካከል ድንበር ክፍት የተደረገ ሲሆን ስሎቫኒያ ለኦስትሪያ በነገው እለት ድንበሯን ትከፍታለች።
~በኮሮና ቫይረስ ቀውስ የተነሳ 42 ሚሊየን አሜሪካውያን ስራ አጥ ነን ሲሉ አመለከቱ።
~ የአፍሪካ ህብረት በቀጣዮቹ ሁለትና ሶስት ወራት ለ10 ሚሊየን አፍሪካውያን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ እቅድ መያዙን አስታወቀ።በአፍሪካ 4,600 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ከ160ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ይገኛሉ።
~ በኢራን በድጋሚ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን ባለፉት ሶስት ቀናት በየእለቱ ከ3 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
~ በፓኪስታን ሁለት የፓርላማ አባላት በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ።በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር 1,688 ሲደርስ ከ83ሺ በላይ ተጠቂዎች ይገኛሉ።
~ የእስራኤል ፓርላማ አባል ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ የምክርቤቱ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተደረገ።
ስምኦን ደረጄ