
ጆቫኒ ሎፔዝ የተባለ በግንባታ ሙያ ላይ የተሰማራ ወጣት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረግህ በሚል በቁጥጥር ስር ሲዉል በፖሊስ የሀይል እርምጃ ተወስዶበታል፡፡የተወሰደበት የሀይል እርምጃ ለሞት ያበቃዉ መሆኑን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣን በሜክሲኮ ፈጥሯል፡፡
ፍትህ ለመጠየቅ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ሲሆን ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል፡፡የሟች ጆቫኒ ሎፔዝ ቤተሰቦች ወደ ሆስፒታል ሲያመሩ የጭንቅላት ጉዳት አጋጥሞት እንደነበረ ተናግረዋል፡፡በእግሩ ላይ በፖሊስ እንደተተኮሰበት ገልፀዋል፡፡
የሜክሲኮ ዜጎች ድርጊቱን ለማዉገዝ የፖሊስ ተሸከርካሪን በእሳት አዉድመዋል፡፡
ስምኦን ደረጄ