~ የጆርጅ ፍሎይድ የተፈጸመበት ግፍ ወካይ ቁጥር #8፡46 ሲሆን ተቃዋሚዎች ፖሊስ በጉልበቱ ጆርጅ ፍሎይድን ለ8 ደቂቃ ከ46 ሰከንድ ረግጧል በሚል የመረጡት ቁጥር ነዉ፡፡
~ በሚችጋን ዲትሮይት የሚገኙ ህንጻዎች ለፍሎይድ አጋርነት በሚል ሀምራዊ ቀለም ያላቸዉን መብራት ከትናንትና ምሽት ጀምሮ አብርተዋል፡፡በፍትህ እጦት የተገደሉትን በሙሉ ይወክላል ሲሉ ገልጸዉታል፡፡
~ የጆርጅ ፍሎይድ ጠበቃ ቤንጃሚን ክራምፕ የዘረንኝነት ወረርሽኝ ዉጤቱ የፍሎይድን ህይወት ቀምቷል ሲሉ ተናገሩ፡፡
~ በሀገረ አሜሪካ በቀጠለዉ ተቃዉሞ በኒዉዮርክ ከተማ ብሩክሊን አደባባይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተቃዉሞአቸዉን በትላንትናዉ እለት አሰሙ፡፡በሪችሞንድ፣በዲሲ፣ቨርጂኒያና ዋሽንግተን በተመሳሳይ ተቃዉሞ ተካሂዷል፡፡
~ ዶናልድ ትራምፕ በሀገረ አሜሪካ የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ እንዲቆም የጦር ሰራዊት አባላት እንዲሰማሩ ማድረጋቸዉ ተገቢነት የለዉም ሲሉ ጄነራል ማርቲን ዲምፕሰይ ተናገሩ፡፡
~ በደቡብ ኮርያ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ዙርያ ፍትህ ይሰጥ ሲሉ ጥያቄ አሰሙ፡፡
~ በአዉስትራሊያ የጆርጅ ፍሎይድ ግድያን ለማዉገዝ በእረፍት ቀናቱ የተጠራዉ የተቃዉሞ ሰልፍ መካሄድ የለበትም ሲሉ ጠ/ሚ ስኮቲ ሞሪሰን ተናገሩ፡፡የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ ዳግም እንዲሰራጭ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ