መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 28፣2012-የደቡብ ሱዳን እውቁ ፖለቲከኛ ጆን ጋራንግ ልጅ ራሳቸውን ከስልጣን አገለሉ

በወርሃ መጋቢት የሀገሪቱ ምክንት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገዉ የተሾሙት ማቢኦር ጋራንግ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ለመልቀቂያቸዉ ምክንያት ደግሞ ፕሬዝዳንት ሳላ ቫኪር እ.ኤ.አ በ2018 የተደረሰበትን የሰላም ስምምነት ለመተግበር ፍላጎት የላቸዉም ሲሉ ሚንስትሩ ወንጅለዋል፡፡

ጋራንግ እንደተናገሩት የደቡብ ሱዳን የሰላም ሁኔታ ከእለት ወደ እለት ወደ ከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡ለአብነትም ባሃር ኢል ጋዛል፣ኢኳቶሪያ፣በናይል፣በአብዬ ግዛቶች የሰላም መደፍረስ እየተባባሰ መምጣቱን አንስተዋል፡፡

በሱዳን ፖለቲካ ዉስጥ ከፍተኛ ስም የነበራቸዉ የጆን ጋራንግ ዲ ማቢኦር ልጅ የሆኑት ጋራንግ ከስልጣን መልቀቃቸዉ ሌላ ቀዉስ እንዳያመጣ ስጋት ወልዷል፡፡

ደቡብ ሱዳን በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርና በተቀናቃኛቸዉ ሪክ ማቻር መካከል በተፈጠረ ዉዝግብ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለህልፈት የዳረገ የእርስ በርስ ቀዉስ ማስተናገዷ አይዘነጋም፡፡

በወርሃ መጋቢት የሀገሪቱ ምክንት የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገዉ የተሾሙት ማቢኦር ጋራንግ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ለመልቀቂያቸዉ ምክንያት ደግሞ ፕሬዝዳንት ሳላ ቫኪር እ.ኤ.አ በ2018 የተደረሰበትን የሰላም ስምምነት ለመተግበር ፍላጎት የላቸዉም ሲሉ ሚንስትሩ ወንጅለዋል፡፡

ጋራንግ እንደተናገሩት የደቡብ ሱዳን የሰላም ሁኔታ ከእለት ወደ እለት ወደ ከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡ለአብነትም ባሃር ኢል ጋዛል፣ኢኳቶሪያ፣በናይል፣በአብዬ ግዛቶች የሰላም መደፍረስ እየተባባሰ መምጣቱን አንስተዋል፡፡

በሱዳን ፖለቲካ ዉስጥ ከፍተኛ ስም የነበራቸዉ የጆን ጋራንግ ዲ ማቢኦር ልጅ የሆኑት ጋራንግ ከስልጣን መልቀቃቸዉ ሌላ ቀዉስ እንዳያመጣ ስጋት ወልዷል፡፡

ደቡብ ሱዳን በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርና በተቀናቃኛቸዉ ሪክ ማቻር መካከል በተፈጠረ ዉዝግብ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለህልፈት የዳረገ የእርስ በርስ ቀዉስ ማስተናገዷ አይዘነጋም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *