መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 29፣2012-በቬትናም የእግርኳስ ዉድድር ከነደጋፊዎች በድጋሚ ተጀመረ፡፡

በወርሃ ግንቦት የጀርመን ቡንደስ ሊጋ እና የደቡብ ኮርያ ኬ ሊግ ያለ ደጋፊ መጀመሩ ይታወሳል፡፡የቬትናም ቪ ሊግ ከ1000ሺ በላይ ደጋፊዎችን በማስተናገድ ዉድድሩ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ተመልካቾች የአፍና አፍንጫ መሸፋኛ ማድረግ ባይገደዱም ሙቀት መለካት ግን ግዴታ ሆኗል፡፡ደጋፊዎች የተመልካች ወንበር ከሚይዘዉ በግማሽ እንዲገቡ ይፈቀዳል፡፡

ቬትናም ከቻይና ጋር ሰፊ ድንበርን ብትጋራም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመመከት በቂ ስራ መስራቷ የስርጭቱ መጠን እንዲቀንስ አድርጋለች፡፡100 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ባላት ቬትናም የቫይረሱ ተጠቂዎች ብዛት 328 ሲሆን ሞት አልተመዘገበም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *