መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 29፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ ብራዚል ከአለም የጤና ድርጅት አባልነት ልትወጣ ትችላለች ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጄር ቦርሴናሮ መናገራቸዉ ተሰማ፡፡የአለም የጤና ድርጅት በፖለቲካ የተጠመደ ስለመሆኑ ቦርሴናሮ ከሰዋል፡፡በብራዚል የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ የመጣ ሲሆን የ35,139 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ የቡድን 20 አባል ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመመከት እንዲቻል የ21 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡የአለማችን 20 የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆኑት ሀገራት የሚለግሱት ገንዘብ ለክትባትና ምርምራ ስራዎች የሚዉል ጭምር ነዉ፡፡

~ በህንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከጣልያን በለጠ፡፡236,657 የቫይረሱ ተጠቂዎችን መለየቷን ህንድ ስታሳዉቅ 6,933 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

~ በስፔን መዲና ማድሪድ የሚገኘዉ የፕራዶ ሙዚየም ለጎብኚዎች ክፍት ተደረገ፡፡በቀን በአማካኝ 15ሺ ሰዎችን የማስተናገድ አቅም ቢኖረዉም አካላዊ ፈቀቅታን ለመጠበቅ ለ1‚800 ብቻ ጎብኚዎች ተፈቅዷል፡፡

~ በኢራን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚዘጋጁ የሰርግ ስነ ስርዓቶች በድጋሚ በሀገሪቱ ቫይረሱ እንዲያገረሽ ምክንያት ሆኗል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ ተናገሩ፡፡

~ በፓኪስታን ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ የ97 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህም ወረርሽኙ በሀገሪቱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡የ1,935 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የተጠቂዎች ቁጥር ከቻይና በመብለጥ ከ93ሺ በላይ ደርሷል፡፡

~ የካዛኪስታን ፕሬዝዳንት ቶካይቪ ቃል አቀባይ ኡሊ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ተሰማ፡፡በካዛኪስታን 2,511 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲኖሩ የ53 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *