የ 31 ዓመቱ አየርላንዳዊው የቀድሞ የማርሻልአርትና ኪክቦክስ ሻምፒዮን (Ultimate Fighting Championship) ኮነር ማክ ግሪጎር 22ት ግዜ ሲያሸንፍ በ 4ቱ ሽንፈት ገጥሞታል።
ከዚህ ቀደም በ 2016 እና በ 2019 ከውድድሩ ዓለም መሰናበቱን ቢያሳውቅም ዳግም ወደ ስፖርቱ ዓለም መመለሱ ይታወቃል።
በወርሃ ጥር ማክግሪጎር አሜሪካዊው ተወዳጅ ዶናልድ ‘ካውቦይ’ ሴሮኒን በላስቬጋስ በ40 ሰከንድ ውስጥ ማሸነፉ ይታወሳል።
ወደቦክሱም ፊቱን በማዞር ከቀድሞው ሻምፒዮን ፍሎይድ ሜይዌዘር ጋር በ 2017 መጋጠሙ በወቅቱ መነጋገሪያ አርጎት ነበር።
ኮነር ማክግሪጎር በትዊተር ገፁ ላይ ከውድድሩ መገለሉን ገልጾ ፤ ለደጋፊዎቹ ምስጋናውን አቅርቧል።
በሚኪያስ ፀጋዬ