መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 30፣2012-አጫጫር መረጃዎች በአሜሪካ ተቃውሞ ዙርያ

~ በኒውዮርክ ቡፋሎ ባሳለፍነው ሁሙስ ለተቃውሞ በወጡ የ75 ዓመት እድሜ ባላቸው አዛዉንት ላይ ጉዳት ያደረሱ ሁለት ፖሊሶች ክስ ተመሰረተባቸው።

~ በደቡብ ኮርያ ታዋቂው የሙዚቃ ባንድ BTS 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ለጥቁሮች መብት መከበር እንቅስቃሴ መለገሱን አስታወቀ።

~ በለንደን ዘረኝነትን ለማውገዝ የጆርጅ ፍሎይድ ግድያን ለመቃወም በተደረገው ሰልፍ 14 የፖሊስ አባላት የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ሪፖርት ተደረገ።

~ 12ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ተቃውሞ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ፣ቺካጎ፣ሎስ አንጀለስና ኒውዮርክ ከተሞች ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

~ በጃማይካ መዲና ኪንግስተን ከተማ በአሜሪካ ኤምባሲ ፊትለፉት በጆርጅ ፍሎይድ ላይ የተፈፀመውን የግፍ ተግባር በማውገዝ ሰልፈኞ ተቃውሞ አሰሙ።

~ የእንግሊዝ የጤና ሚንስትር ማት ሀንኩክ የፍሎይድን ግድያ ለማውገዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በለንደን አደባባይ መውጣታቸው የኮሮና ቫይረስ መዛመት ስጋትን ጨምሯል ሲሉ ተናገሩ።

~ በፍሎሪዳ በሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ የጎልፍ ሪዞርት በራፍ ላይ 100 የሚሆኑ ሰዎች ተቃውሞ አሰምተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *