
~ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የአየር መንገድ ኢንዱስትሪ የ82 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ እንደሚያጋጥመዉ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር(IATA) አስታወቀ፡፡
~ ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመመከት ከኩባ ለመጡት የህክምና ባለሙያዎች 14 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደምትከፍል አስታወቀች፡፡የህክምና ባለሙያዎቹ እስከ ቀጣይ ዓመት ይቆያሉ፡፡
~ ቻይና በአዉስትራሊያ ለመማር የሚገልጉ ዜጎቿ የዘረኝነት ጥቃት ሊደርስባቸዉ ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክር ለገሰች፡፡በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሰሞን እስያ ጠል ጥቃት በአዉስትራሊያ ሲፈጸም እንደነበር ቻይና አሳዉቃለች፡፡አዉስትራሊያ የቻይናን መልዕክት አስተባብላለች፡፡
~ በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ በአምስት ሆስፒታሎች የህክምና ድጋፍ እንዲደረግለት ትብብር ቢጠይቅም ይህ ሳይሳካ በመቅረቱ ህይወቱ አልፏል፡፡ድርጊቱ ህንዳዉያኑን እያስቆጣ ይገኛል፡፡
~ ፈረንሳይ የአቬሽን ኢንዱስትሪዋን ለመደገፍ የ16.9 በሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡በዚህም የአዉሮፕላን አምራቹ ኤርባስ እና የፈረንሳይ ብሄራዊ አየር መንገድ ኤር ፍራንስ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
~ ቬንዞዌላ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ ከኢራን እንደተደረገላት አስታወቀች፡፡ሁለቱ በነዳጅ የበለጸጉ ሀገራት በአሜሪካ ማዕቀብ እንደተጣለባቸዉ ይታወቃል፡፡
~ ሰሜን ኮርያ በኮሮና ቫይረስ ቀዉስ የተነሳ ድንበሯን ለቻይና መዝጋቷን ተከትሎ የምግብ እጥረት ማጋጠሙ እና ዜጎች ለረሃብ መጋላጣቸዉን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ተቋም አስታወቀ፡፡
ስምኦን ደረጄ