
የአይኤስ አባል የነበረዉ ሞሃመድ ሁስኒ ሳዑድ የተባለዉ ግለሰብ ለእንግሊዝ የደህንነት መስሪያ ቤት ቅጥረኛ በመሆን በሶርያ ስለሚገኘዉ የሩሲያ የጦር ሰፈር መረጃ አሳልፎ ይሰጥ እንደነበር ተናገረ፡፡የተሰጠዉን ተልዕኮ ለማሳካት ከዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ድጋፍ ይደረግለት እንደነበረም ተናግሯል፡፡
በሶርያ ዮርዳኖስ ድንበር አቅራቢያ የመረጃ ልዉዉጥ ያደርግ እንደነበረም ግለሰቡ ይፋ አድርጓል፡፡ከእርሱ በተጨማሪ በሶርያ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉ የቀድሞ የአይኤስ አባላት ከእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ ያገኙ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ስምኦን ደረጄ