መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 3፣2012-የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ድርድር ዛሬም ይቀጥላልየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የሙሌትና ዓመታዊ የውሃ አለቃቀቅ በተመለከተ በኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬም ይቀጥላል።


በግድቡ የሙሌትና ዓመታዊ የውሃ አለቃቀቅ ላይ በኢትዮጵያ ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ትናንት ምሽት በበይነ-መረብ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
በውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ በተካሄደው በዚህ ድርድር ደቡብ አፍሪካ ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ በታዛቢነት ተሳትፈዋል።
በዚህ ስብሰባ አገራቱ የድርድር ስነ-ስርዓትን ፣ ታዛቢዎችን ፣ ስለ ድርድሩ አካሄድና ዋናዋናበድርድሩ ያልተቋጩ ጉዳዮችን በተመለከተ ተነጋግረዋል።
እያንዳንዱ አገር ዋናዋና የድርድር ጉዳዮች ናቸው ያላቸውን ሃሳቦች በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ተከታታይ ውይይቶችን ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ይሁን እንጂ የታዛቢዎቹ ሚና ምን ይሁን የሚለውን በተመለከተ በአገራቱ መካከል መግባባት ላይ አልተደረሰም።
ስብሰባው ዛሬም የሚቀጥል ሲሆን የሶስቱ አገራት ድርድር የግድቡ የመጀመሪያ ሙሌትና ዓመታዊ አለቃቀቅ ላይ ብቻ የተወሰነ ይሆናል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ልዩነቶችን በድርድር ለመፍታት ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ዝግጁ ናት ሲል የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *