መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ባለፉት 20 ቀናት አስቀድሞ ከተመዘገበው በእጥፍ መጨመሩን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።በአፍሪካ ከ200ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲለዩ ከ5ሺ በላይ ሞት ተመዝግቧል።

~ በአሜሪካ 20 ግዛቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመሩ ተስማ።ኒውዮርክን ጨምሮ በሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች የቫይረሱ የስርጭት መጠን ቢቀንስም በካሊፎርኒያ፣ቴክሳስ፣ዋሽንግተን፣ደቡባዊ ካሮላይና እና በጥቅሉ 20 ግዛቶች ላይ ስርጭቱ በመጨመር ላይ ይገኛል።

~ ግብፅ ከ12 ቀናቶች በኃላ አንዳንድ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎቿን ለጎብኚዎች ክፍት ታደርጋለች ተባለ።በቀይና በሜድትራኒያን የባህር ዳርቻ መዝናኛዎች ክፍት ይደረጋሉ ተብሏል።

~ በዩናይትድ ስቴትስ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ስራ አጥ ነን ያሉ ዜጎች ቁጥር 44.2 ሚሊየን ደረሰ።ባለፈው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ 1.5 ሚሊየን አሜሪካውያን ስራ አጥ ስለመሆናቸው አመልክተዋል።

~ ቻይና ስለ ኮሮና ቫይረስ መዛመት በቂ መረጃ ሳትሰጥ ቫይረሱ እንዲስፋፋ አድርጋለች በሚል በአውሮጳ ህብረት የቀረበባትን ክስ ሀሰተኛ ስትል ምላሽ ሰጠች።

~ ታይላንድ ከሶስት ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ አዲስ ተጠቂም ሆነ ሞት አለመመዝገቡን ይፋ አደረገች።በታይላንድ 3,125 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲለዩ የ58 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ ማሌዥያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሀጅ ጉዞ እንዳያደርጉ መመሪያ አስተላለፈች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *