
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የፌዴራል መንግስት የ2013 ረቂቅ በጀት በተመለከተ በሚያቀርቡት የበጀት መግለጫ በማድመጥ ላይ ይገኛል፡፡
ረቂቅ በጀቱም ብር 476 ቢሊዮን ሆኖ ለምክር ቤቱ ውይይት ቀርቧል፡፡
የ2013 በጀት ግብዓትን ከውጤት ጋር የሚያዛምድ እንዲሁም ኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ኢኮኖሚው በ8 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብም የገንዘብ ሚነስትሩ መናገራቸውን ከምክር ቤቱ ማህበራዊ ድረገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡