መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-በአሜሪካ የሚገኙ ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ የተጠቃች ሴትን የተሳካ የሳምባ የንቅለ ተከላ ህክምና ማድረጋቸው አድናቆት እያስቸራቸው ይገኛል

በአሜሪካ ቺካጎ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ሁለቱም ሳምባዎቿ ከጥቅም ውጪ ለሆነች ታማሚ ከለጋሽ በተሰጠ ሳምባ የንቅለ ተከላ ህክምና ተደርጎላታል።በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የምትገኘው ወጣት በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ለስድስት ሳምንታት በፅኑ የህሙማን መከታተያ በአጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ እንድትተነፍስ ሲደረግ ቆይቷል።

በኮሮና የተጠቃ ሰው የሳምባ ጤና በከፍተኛ ደረጃ የሚቃወስ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ የንቅለ ተከላ ህክምና ማድረግ መቻሉ ባለሙያዎቹን እያስመሰገነ ይገኛል።የሳምባ የንቅለ ተከላው ህክምና ሂደት 48 ሰዓታትን የፈጀ ሲሆን ሁለቱንም ሳምባዋ እንዲንቀየር ተደርጓል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *