
በኢንዶኔዥያ በሚገኙ ሆስፒታሎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዉ ህይወታቸዉ ያለፉ ሰዎች ቤተሰቦች በራሳችን የቀብር ስነስርዓት እንፈጽማለን በሚል የአስክሬን ስርቆት የፈጸሙ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡ ቢያንስ 33 ተጠርጣሪዎች መያዛቸዉ ተረጋግጧል፡፡
ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጥፋተኛ ሆነዉ ከተገኙ የ7 ዓመት እስር እና ከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ ይጠብቃቸዋል፡፡በኢንዶኔዥያ 34,316 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲገኙ የ2,356 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ