መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ በቻይና እየተሰራ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድኃኒት በጦጣ ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጪ ውጤት አስገኘ።በቀጣይ 1000 በጎ ፍቃደኞች ላይ ሙከራ ለማድረግ በሂደት ይገኛል።

~ የዋሽንግተን ዲሲ የብሄራዊ ዘብ በርካታ አባላት በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰማ።ቫይረሱ ሊስፋፋ የቻለው ከፍሎይድ ግድያ ጋር በተያያዘ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ እንደሆነ ታውቋል።

~ የጣልያን ጠቅላይ አቃቢ ህግ የጣልያን መንግስት ሀላፊዎች እና ጠቅላይ ሚንስትር ኮንቴን የፊታችን አርብ በቤርጋሞ የኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ ጥፋት ለምን ሊያደርስ ቻለ በሚለው ዙርያ ለጥያቄ እንደሚፈልጋቸው ይፋ አደረገ።

~ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የነበሩት የቤልጄየም ልዑል ጆአኪም እንቅስቃሴ የሚከለክለውን ህግ በመጣስ ወደ ስፔን በማምራት በቫይረሱ በመያዛቸው 11,800 የአሜሪካን ዶላር ይቀጣሉ ተባለ።

~ በዩራጋይ ከሶስት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሱቆች ክፍይ ተደረጉ

~ በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺ በለጠ።202,782 ሰዎች በመላው አፍሪካ በቫይረሱ ተይዘዋል።የ5,516 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ሲደረግ ከ90ሺ በለይ የቫይረሱ ህሙማን ከቫይረሱ አገግመዋል።

~ በኢራን በድጋሚ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን ባለፉት ሶስት ቀናት በየእለቱ ከ3 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

~ በኮሮና ቫይረስ ቀውስ የተነሳ በቀጣዮቹ ወራት 800ሺ ሰዎች በፈረንሳይ ከስራ ገበታቸው ውጪ እንደሚሆኑ ተጠቆመ።

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *