
በህገወጥ መንገድ የታረደ የ50 ከብት ስጋ እና ከ360 በላይ የበግ እና የፍየል ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉንና በ132 ልኳንዳ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገልጿል፡፡
የተወሰኑ ስጋ ቤቶች አንድ በሬ በቄራዎች ድርጅት እርድ ካከናወኑ በኋላ በዚህ ሽፋን ተጨማሪ በሬዎችን ከቄራዎች ድርጅት እንደታረዱ በማስመሰል ህገወጥ ስጋ ለህብረተሰቡ ሊሸጡ መገኘታቸውን ተጠቁሟል፡፡
በዚህ ተግባር የተሳተፉ በርካታ ግለሰቦች እና የልኳንዳ ቤት ባለንብረቶች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡