በቦርኖ ግዛት ሞንጉኖ በተባለው ስፍራ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ቢያንስ 20 ወታደሮች እና ከ 40 በላይ ንፁሃን መገደላቸው ተሰምቷል፡፡
ከቦኮሃራም ተገንጥሎ የወጣው የምዕራብ አፍሪካ እስላሚክ እስቴት የተባለው ቡድን ለጥቃቱ ላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡
ይህ ቡድን ከቦኮሃራም ከተገነጠለ 4 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ ባለፈው ሳምንት ጉቢዮ በተባለች ስፍራ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 81 የናይጄሪያ ዜጎች ህይወታቸውን ማጣታቸው አይዘነጋም፡፡ ከ 10 ዓመት በላይ በዘለቀው ቀውስ የተነሳ ከ 100 ሺህ በላይ የሞንገኖ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ