መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 8፣2012-በኬንያ የሚገኙ ፖሊሶች የኮሮና ቫይረስ መመሪያን ለማስፈፀም መጠነ ሰፊ የሀይል እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ ተሰማ

በመዲናዋ ናይሮቢ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ በፖሊስ የሀይል እርምጃ ህይወቱን ሲያጣ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የሆነ ግለሰብ ደግሞ በፖሊስ እርምጃ የአይን ብርሃኑን ማጣቱ ሪፖርት ተደርጓል።

ፖሊስ እየቀረበበት ያለውን ውንጀላ ቢያስተባብልም በገለልተኛ አካል በተደረገ ማጣራት ቢያንስ 15 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር የወጡ መመሪያዎችን በሚያስፈፅሙ የፖሊስ አካላት ህይወታቸውን ተነጥቀዋል።

በሌላ የኬንያ መረጃ በኬንያ ፕሬዝዳንት ኧሁሩ ኬንያታ ጽህፈት ቤት የሚሰሩ አራት ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ ስለመጠቃታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *