ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ነበር ለውይይቱ ጅቡቲ የገቡት። በሶማሊያ እና በሶማሌላንድ ግንኙነት ዙሪያ በጅቡቲ የተካሄደው የምክክር ጉባኤው በየካቲት 2012 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ የተደረገው ውይይት ተከታይ ክፍል ነው።
በዚሁ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ዕርቅን ማውረድ ለቀጠናው ውህደት መሠረት እንደሆነ መግለፃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃ አመላክቷል።