መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 9፣2012-አጫጭር መረጃ ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር በተያያዘ በቀጠለዉ ተቃዉሞ ዙርያ

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን ሀሙስ የሀገሪቱ ፖሊስ በአፍሪካ አሜሪካዉያን ላይ ያለዉን አያያዝ እንዲያሻሽል የሚያደርግ የአስፈጻሚ አካል መመሪያን ይፈርማሉ፡፡

በአትላንታ ፖሊስ ሬይሻርድ የተባለ ግለሰብ ከሶስት ቀናት በፊት መገደሉን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃዉሞ መደረጉን ቀጥሏል፡፡ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር በተያያዘ ከባድ ተቃዉሞ ዉስጥ የሰነበተችዉ አትላንታ በፖሊስ እጅ የሌላ ግለሰብ ህይወት መጥፋቱ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

የአትላንታ የፖሊስ ፋዉንዴሽን እንዳስታወቀዉ ባለፉት 15 ቀናት ዉስጥ ብቻ ስምንት የፖሊስ አባላት ስራቸዉን መልቀቃቸዉን ይፋ አድርጓል፡፡ዝርዝር መረጃ ባይገለጽም አጋርነታቸዉን ለሰልፈኞች ለማሳየት ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

የጥቁም መበት አቀንቃኝ የሆነች ግለሰብ በፍሎሪዳ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የኬንታኪ ግዛት ገዢ ኒድ ላሞንት ፖሊስ የተጠርጣሪን አንገት አንቆ መያዝ በግዛቲቱ መያዝ እንደማይቻል ይፋ አደረጉ፡፡የሎስ አንጀለስ ዩኒፋይድ ትምህርት ቤቶች አዉራጃ ፖሊስ የተጠርጣሪን አንገት መያዝና አስለቃሽ ጋዝ ከመጠቀም ታገደ፡፡

በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ህይወታቸዉ ባለፉ ሁለት ጥቁሮች ዙርያ ኤፍ ቢ አይ ምርመራ ማድረግ ጀመረ፡፡ግለሰቦቹ የ24 ዓመቱ ሮበርት ፉለር እና የ38 ዓመቱ ማልኮም ሀርሲች ይባላሉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *