መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 10፤2012-ህንድ እና ቻይና በመካከላቸው ለነበረው የተኩስ ልውውጥ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ይገኛል፡፡

በሂማላያን አካባቢ ቢያንስ 20 የህንድ ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ ፀብ ጫሪ ተኩስ አስቀድማ የጀመረችው ቻይና ናት ስትል ህንድ ስትከስ ፤ ቻይና በበኩሏ የህንድ ትኮሳ ነው ስትል ተናግራለች፡፡

የህንድ ጦር በበኩሉ በርካታ ወታደሮቹ ክፉኛ እንደተጎዱ ገልጿል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ደም አፍሳሽ የተኩስ ልውውጥ በላዳክህ ግዛት ሲደረግ ከ 45 ዓመት በኋላ የአሁኑ የመጀመሪያ ነው፡፡

በላዳክህ ግዛት አካባቢ ህንድ አዲስ መንገድ የገነባች ሲሆን ይህ ለቤጂንግ አልተዋጠላትም፡፡ በሀገራቱ መካከል ግጭት እንኳ ቢፈጠር ዴልሂ ሰውና እቃዎችን በፍጥነት ለማጋዝ ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ጥርጣሬም አላት፡፡

ሁለቱም ሀገራት የኒውክሌር የጦር መሳሪያ እንደታጠቁ ይታወቃል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *