
~ በቱኒዚያ በሺዎች የሚቆጠሩ የህክምና ባለሙያዎች አደባባይ በመውጣት የተሻለ የጤና ስርዓት ያስፈልጋል ሲሉ ተቃውሞ አሰሙ።የቫይረሱ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ መሰል ተቃውሞ በጣልያንና ፈረንሳይ መደረጉ ይታወሳል።
~ የኔፓል መንግስት የኮሮና ቫይረስ ምላሽ ደካማ ነው ሲሉ ከሀገሪቱ ዜጎች ጋር አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ ያሰሙ የውጪ ሀገራት ዜጎች ከኔፓል ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ።3 የቻይና፣1 የአሜሪካና 1 የአውስትራልያ ዜጎች ናቸው
~ በባንግላዲሽ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ100ሺ በለጠ።በመላው ባንግላዲሽ 102,292 የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲለዩ የ1,343 ሰዎች ህይወት አልፏል።በየእለቱ ከ3ሺ ያላነሱ ዜጎች በቫይረሱ እየተጠቁ ይገኛል።
~ ዴንማርክ ከስውዲን እና ፖርቹጋል በስተቀር ለአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ድንበሯን ክፍት አደረገች።ሁለቱ ሀገራት ከ100ሺ ሰው በአማካይ ከ20 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባቸው ናቸው በሚል የዴንማርክን መስፈርት አላሟሉም ተብሏል።
~ እንግሊዝ እና አውስትራሊያ የኮሮና ቫይረስ ትክክለኛ የመነሻ ስፍራ የት እንደሆነ በገለልተኛ አካል ሊጠና ይገባል ብለዋል።ሀገራቱ በዚሁ ዙርያ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።
~ በካዛኪስታን ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኑርሱልጣን ናዛራባይቪ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰማ።የ79 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከ30 ዓመት የስልጣን ቆይታ በኃላ በገዛ ፍቃዳቸው ባለፈው ዓመት ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።
~ በራሺያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ 489 የህክምና ባለሙያዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ሪፖርት ተደረገ።በራሺያ በቫይረሱ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች 6 በመቶ ድርሻ ያላቸው የህክምና ባለሙያዎች ናቸው።
በስምኦን ደረጄ