የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ፍጥነት መዛመት መቀጠሉን ይፋ አድርገዋል።በትላንትናው እለት ብቻ በመላው ዓለም በ24 ሰዓት ውስጥ 150 ሺ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል።
ይህንኑ ተከትሎ ቫይረሱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ የቫይረሱ መዛመት የተመዘገብበት ቀን ስለመሆኑ ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል።ከተመዘገበው የቫይረሱ ተጠቂዎች ግማሽ በመቶ በአሜሪካ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።
በስምኦን ደረጄ