መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2012-ሶማሊያ በትራምፕ ንግግር ዙርያ ዝምታን መርጣለች

ቅዳሜ ምሽት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2020 የምረጡ ዘመቻቸው ላይ ለሶማሊያ አሜሪካዊቷ የኮንግረሱ አባል ኢላን ኦማር ላይ ትችት ሰንዝረዋል።

የአሜሪካ መንግስትን ልክ እንደመጣችበት ሀገር እንዲሆን ትፈልጋለች ሲሉ ተናግረዋል።ሶማሊያ ማለት መንግስት የሌላት፣ምንም ደህንነት የማይታይበት፣ፖሊስ ሆን ፀጥታ ያልሰፈነባት ስርዓት አልበኛ ሀገር ናት ሲሉ ትራምፕ ገልፀዋታል።

የሶማሊያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በትራምፕ በተሰነዘረው ትችት ዙርያ ዝምታን መርጧል።ትራምፕ ኢላን ኦማርን በጥላቻ የተሞላች ነች ብለዋል።

ኢላን ኦማር ትራምፕ ዘረኛ ነው ማለቷን ተከትሎ በዶናልድ ትራምፕ የትችት ጥርስ ውስጥ ገብታለች።ኢላን ኦማር በሶማሊያ የእርስ በእርስ ቀውስ ወቅት ሀገሯን ለቃ ከቤተሰቦቿ ጋር የወጣች ሲሆን አራት አመት በኬንያ የስደተኞች የመጠለያ ጣቢያ ካሳለፈች በኃላ እ.ኤ.አ በ1995 አሜሪካ መግባት ችላለች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *