መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2012-የማሌዥያ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ከቤት ያለመውጣት መመሪያን ተከትሎ ክብደታችን እየጨመረ ነው ሲሉ ቅሬታ አሰሙ

ከመጋቢት አጋማሽ አንስቶ በኳላላምፑር ከቤት መውጣት ያቆሙ ዜጎች ክብደታቸው መጨመሩን THE STAR የተሰኘ ጋዜጣ ለንባብ አብቅቷል፡፡

አንዳንዶች ክብደታቸው በመጨመሩ የተነሳ በማህበራዊ ገፅ ትስስር ምስላቸውን ለማጋራት ሀፍረት እንደተሰማቸው ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡

ማሌዥያ በከፍተኛ የክብደት መጠን ዜጎቿ የሚሰቃዩባት ሀገር ስትሆን በደቡብ ምስራቅ እስያ ከሚገኙ ሀገራት ቀዳሚ በመሆን 15.6 በመቶ ዜጎቿ በከባድ ውፍረት ይሰቃያሉ፡፡

በማሌዥያ ከሚገኙ አዋቂዎች 50በመቶ ያህሉ በከፍተኛ እና ቅጥ ባጣ ውፍረት ውስጥ እንደሚገኙ የስታር ዘገባ አመላክቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *