መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2012-የራሺው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቀጣዩ ምርጫ እንደሚሳተፉ ፍንጭ ሰጡ

በሩሲያ ባለው ህግ መሰረት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የስልጣን ዘመናቸው እ.ኤ.አ በ2024 ያበቃል።ሆኖም ግን ይህንን ህግ ለማሻሻል በሀምሌ 1 በራሺያ ድምፅ የሚሰጥበት ሲሆን ፑቲን እስከ 2036 በስልጣን ላይ እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸው ነው።

ህገ መንግስቱ እንዲሻሻል በህግ አውጪዎቹ እና በራሽያ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ውሳኔ ማግኘቱ አይዘነጋም።ይህንኑ ተክትሎ የ67 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሀምሌ 1 ውሳኔ ካገኘ በድጋሚ ይወዳደራሉ።

ፑቲን እ.ኤ.አ ከ2000 እስከ 2008 እና ከ2012 ጀምሮ ራሺያን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ የሚገኝ ሲሆን ከ1999 እስከ 2000 እና ከ2008 እስከ 2012 ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትርነት አገልግለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *