መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 17፤2012-በቀጣይ ሳምንት ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት እቅድ ይዛ የነበረችው ላይቤሪያ የትምህርት ሚንስትሩ እና ምክትላቸው በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

ላይቤሪያ ለሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች በቀጣዩ ሰኞ ትምህርት ቤቶችን እንደምትከፍት ይፋ አድርጋ ነበር።ሆኖም የትምህርት ሚንስትሩ አንሱ ሶኒ እና ምክትል ሚንስትሩ ላቲም ዳ ቶንግ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ስጋት ፈጥሯል።

ምክትል ሚንስትሩ የጤናቸው ሁኔታ ተባብሶ ወደ ጋና ማምራታቸው የታወቀ ሲሆን ሚንስትሩ አንሱ ሶኒ ወደ ጋና አምርተዋል መባሉን የላይቤሪያ የመረጃ ሚንስቴር መረጃውን አስተባብሏል።

በላይቤሪያ 652 የኮሮና ቫይረስ መኖራቸው ሲመዘገብ የ34 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *