መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 17፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ ለኮሮና ቫይረስ የተመደበን ገንዘብ መዝብረዋል የተባሉት የዚምባብዌ የጤና ሚንስትር በቁጥጥር ስር ዋሉ።ሚንስትሩ ዶ/ር ቺታሉ ቺሉፋ አራት የክስ መዝገብ ከምዝበራ ቅሌት ጋር በተያያዘ ቀርቦባቸዋል።

~ በኢራቅ ከፍተኛ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ባለፉት 24 ሰዓት ተመዘገበ።በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በኢራቅ 2,200 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ አጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 36,702 ደርሷል።1,330 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

~ የአለም የጤና ድርጅት በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ መቻሉን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል።

~ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(IMF)የ2020 የዓለም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ 5 በመቶ እንደሚቀንስ ትንበያውን ይፋ አደረገ።ተቋም በወርሃ ሚያዚያ የአለም ኢኮኖሚ ሊያጋጥመው ይችላል ካለው ጉዳት የአሁኑ ትንበያ በ2 በመቶ የበለጠ ነው።

~ በብራዚል በ24 ሰዓት ውስጥ የ1,374 ሰዎች ሞት በኮሮና ቫይረስ የተነሣ ተመዘገበ።የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በሀገሪቱ ከ1.1 ሚሊየን በላይ ደርሷል።

~ የኳታር አየርመንገድ ከቀጣዩ ሳምንት አንስቶ በየእለቱ ወደ ሊባኖስ መዲና ቤሩት ከተማ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።

~ የአለም የጤና ድርጅት በቀጣዩ ሳምንት በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 10 ሚሊየን ሊደርስ እንደሚችል አስታወቀ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *