መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 22፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በጋና የኮሮና ቫይረስ መድሃኒት በሚል ሀሰተኛ መድሃኒትን እስከ 150 የጋና የመገበያያ ገንዘብ እየተሸጠ ይገኛል።በአፍሪካ በየዓመቱ በሀሰተኛ መድሃኒት የተነሳ የ100ሺ ሰዎች ህይወት እንደሚያልፍ የአለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

~ በኢራን በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዘገበ።ባለፉት 24 ሰዓት 162 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቫይረሱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።በአጠቃላይ በኢራን 10,670 ሞት ሪፖርት ተደርጓል።

~ ኬንያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ከቱሪዝም ማግኘት የነበረባትን 751 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማጣቷን አስታወቀች።ከኬንያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ከምታገኘው ገቢ በመቀጠል ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬን ገቢን ኬንያ የምታገኘው ከቱሪዝም ነው።

~ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ ሰዎች መካከል ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች የተመዘገበው በምስራቃዊ ሜድትራኒያ ባሉ ሀገራት መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።ሀገራቱኢራቅ፣ኢራን፣ሊቢያ፣ሞሮኮ፣ፍልስጤም፣ፓኪስታን እና ኦማን ናቸው።

~ በአሜሪካ ከሚገኙ ግዛቶች መካከል በ36ቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርይ አደረገ።

~ ታይላንድ ላለፉት 35 ቀናት በሀገር ውስጥ የኮሮና ቫይረስ መዛመት አለመመዝገቡን ይፋ አደረገች።ከውጪ ሀገራት በመጡ ዜጎች ላይ ብቻ ቫይረሱ መገኘቱን አስታውቃለች።

~ በህንድ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ 100ሺ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቁ።ከ548ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሪፖርት በተደረገባት ህንድ ከነዚህ መካከል 312ሺ አገግመዋል።የ16,475 ሰዎች ህልፈት ይፋ ተደርጓል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *