መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 20፣2012-በቬትንሀም ከ 30 ዓመታት በኋላ በትምህርት ቤታቸው ዳግም ለመዋሀድ ሲጓዙ የነበሩ ጓደኛሞች፤ የሚጓዙበት አውቶቡስ ተገልብጦ 13ቱ ሕይወታቸው አልፏል

አደጋው የደረሰው በቬትንሀም ቋንግ ቢንህ አውራጃ ሲሆን፤ቀድሞ በዶንግ ሆይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ዳግም ለመሰባሰብና 30ኛ ዓመት ምርቃታቸውን ለማሰብ ወደ ትምህርት ቤቱ በአውቶቡስ ሲጓዙ በነበረበት ወቅት ነው፡፡

በአደጋው 13ቱ ወድያው ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ ጉዳት አጋጥሟቸዋል፡፡

በቬትንሀም ጎዳናዎች ማሽከርከር ከባድ መሆኑንና ከ15 እስከ 29 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙቱ ለህልፈታቸው ዋነኛ ምክንያት ስለመሆኑም የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሣያል፡፡

በ2020 ዓመት 6 ወራት ብቻ 3200 የሞት አደጋ ማጋጠሙን ሀገሪቱ ይፋ አድርጋለች፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *