መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 20፣2012-በኢትዮጵያ በ2012 በጀት ዓመት በትራፊክ አደጋ 3400 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት የትራፊክ አደጋን በ17 በመቶ መቀነስ መቻሉን የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ-አዳማ የፍጥነት መንገድ መግቢያ ላይ “የትራፊክ አደጋ ሰለባዎችን እያሰብን አረንጓዴ አሻራችንን እናኑር!” በሚል መሪ ቃል የትራፊክ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች በተገኙበት ደም የመለገስ እና የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሐ ግብር ተከናውኗል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት በ2011 በጀት ዓመት የተመዘገበው 4597 ሞት በ2012 በጀት ዓመት ወደ 3400 መቀነሱን አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *