መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 20፣2012-በ2012 በጀት ዓመት ከ312 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ

ከጉምሩክ ኮሚሽን በተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ኮኬን ፣ ካናቢስ እና ሌሎች ከፍተኛ መጠን ያላቸው አደንዛዥ ዕፆች በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማስወጣት ሲሞከሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ከተያዙት አደንዛዥ ዕፅ ዓይነቶች ውስጥ 14ሺ785 ኪ.ግ ካናቢስ ፣ 1ሺ976 ኪ.ግ ኮኬይን እና 7ሺ 622 ኪ.ግ ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች ይገኙበታል፡፡

ከዚህ ውስጥ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረው አደንዛዥ ዕፅ ዋጋ ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ ይገመታል፡፡

በተጨማሪም በኮንትሮባንድ ከሀገር ሊወጣ የነበረው የአደንዛዥ ዕፅ ዋጋ ደግሞ ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት እንዳለው በገቢዎች ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *