መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፣2012-ምስጋና ለኒዉክሌር ጦር ሀይል ይሁን እና ጦርነት አይኖርም ሲሉ የሰሜን ኮርያዉ መሪ ኪም ጂንግ አን ተናገሩ

በዛሬዉ እለት በሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ መልዕክታቸዉን ያስተላለፉት የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ አን የኒዉክሌር የጦር ሀይል መተማመኛ በመሆኑ የተነሳ ጦርነት አያሰጋንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኪም መዕክታቸዉን ያስተላለፉት እ.ኤ.አ ከ1950 እስከ 53 የተካሄደዉ የኮርያ ጦርነት ያበቃበትን 67 ዓመት የመታሰቢያ በዓልን በማስመልከት ነዉ፡፡ሀገራቸዉ የዩራኒየም ማበልጸግ ተግባርን በማከናወን የኒዉክሌር ሀይል ባለቤት የሆነችዉ ለማሸነፍ ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከኢምፔራሊስቶች የሚሰነዘርብንን ማንኛዉንም ጥቃት አሁን ላይ የመመከት ሙሉ አቅም አለን ሲሉ ኪም ጆንግ አን ተናግረዋል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *