መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፣2012-የቀድሞ የማሌዥያ ጠ/ሚ ናጂብ ራዛቅ በቀረበባቸዉ ሰባት የክስ መዝገቦች ጥፋተኛ ተባሉ

ጠ/ሚ ናጂብ ራዛቅ በስልጣን መንበር ላይ በነበሩበት ጊዜ የአንድ ማሌዥያ የልማት ፕሮጀክት ይፋ ቢያደርጉም ከፕሮጀክቱ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ ስለመጥፋቱ የማሌዥያ አቃቢ ህግ አስታዉቋል፡፡ናጂብ በዛሬዉ እለት በኳላ ሉምፑር ፍርድ ቤት ሲደርሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎችቸዉ አደባባይ በመዉጣት የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ለዘላለም ይኑሩ ሲሉ ድጋፍ አሰምተዋል፡፡

ናጂብ የቀረበባቸዉ ክስ የፖለቲካ መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ በዛሬዉ እለት ምንም ወሰነ ምን የጎደፈዉን ስሜን ለማጥራት ይጠቅመኛል ብለዋል፡፡ናጂብ በተከሰሱበት የምዝበራ ቅሌት ጥፋተኛ መባላቸዉን ተከትሎ ከ15 እስከ 20 ዓመታት ሊደርስ በሚችል እስር ይቀጣሉ፡፡

የፖለቲካ ሰማያዊ ደም አለባቸዉ የሚባሉት ናጂብ ራዛቅ ወላጅ አባታቸዉ አብዱል ራዛቅ ሁሴን የማሌዥያ ሁለተኛዉ ጠቅላይ ሚንስትር ነበሩ፡፡እንዲሁም ሶስተኛዉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት አጎታቸዉ ነበሩ፡፡

ስልጣናቸዉ በ2018 ያበቃዉ 6ኛዉ የማሌዥያ ጠቅላይ ሚንስትር ናጂብ ራዛቅ በፖሊስ በመኖሪያ ቤታቸዉ በተደረገ ፍተሻ 1400 የአንገት ሀብል፣567 ቅንጡ የእጅ ቦርሳ፣423 ሰዓት፣2200 ቀለበቶች በጥቅሉ 273 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ዉድ ቁሳቁስ ሊገኝ ችሏል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *