መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 22፣2012-በሶማሊያ የኢንተርኔት መቋረጥ ከፖለቲካው ጋር ተያያዥነት እንደሌለው መንግስት አስታወቀ

በሀገሪቱ ባሳለፍነው ሰኞ የኢንተርኔት አገልግሎት ቢቋረጥም በትላንትናው እለት በድጋሚ መመለሱ ይታወሳል፡፡

የሶማሊያ የቴክኖሊጂ ሚንስቴር አብዲ አሹሩ ሃሰን በኢንተርኔት ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰ ጉዳት የተፈጠረ ነው ብለዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ መንግስት እና በሶማሊያ የኢንተርኔት አቅራቢው ዳልኮም በጋራ ሁኔታውን እንደሚያጣራ ገልፀዋል፡፡

ከሶማሊያ ባህር ዳርቻ 27ኪ.ሜ ርቀት ላይ የኢንተርኔት ማስተላለፊያ መስመር ላይ እንዴት ሊቋረጥ እንደቻለ ይጣራል ተብሏል፡፡

መንግስት ይህንን ይበሉ እንጂ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አል ኬሀሪ ከስልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ውጥረት እንዳይነግስ ኢንተርኔቱ ተቋርጧል የሚለውን ይቀበላሉ፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *