
የቢቢሲ የፐርሺያ የዜና አገልግሎት በሰራው የምርመራ ዘገባ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን እንዳጡ በኢራን የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ከተደረገው በሶስት እጥፍ እንደሚበልጥ ማረጋገጥ ችለናል ሲል ጽፏል፡፡
ኢራን መረጃውን ለመሸሸግ የፈለገችው እ.ኤ.አ በ 1979 የነበረውን አብዮት እና የፓርላማ ምርጫ ለማካሄድ በሚል የቫይረሱን ስርጭት በመንግስት ትኩረት ሣይሰጠው ቀርቷል፡፡
በኢራን የጤና ሚኒስቴር በኩል በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ 17ሺ የበለጠ አይደሉም ቢልም ቢቢሲ 42ሺ ሰዎች በኢራን በቫይረሱ ህይወታቸው አልፏል ብሏል፡፡