መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 27፣2012-በኢትዮጵያ ተጨማሪ 26 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ሲያልፍ 583 ሰዎች በተህዋሲው ተጠቅተዋል

በትናንትናው እለት ለ6907 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 583 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ተጨማሪ 26 ሰዎችም ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡330 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 19,289 ፣ ያገገሙት 7931፣ የሟቾች ቁጥር 336 ሲደርስ ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 145 ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *