
አቶ ልደቱም ለጉብኝቱ ከልብ በማመስገን ዋናው ችግር የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት መሆኑን አስረድቷል።
የሰብዓዊ መብት ባለስልጣናት ለጉብኝት ይመጣሉ መባሉ እንደተሰማ በኮሮና ታመዋል የተባሉትን ግለሰቦች ከእስር ቤት አስወጥተው ሌላ ቦታ እንደወሰዷቸውም ለኮሚሽነሩ ገልጾላቸዋል።
ኢዴፓ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን ፤ ኮሚሽኑ የአቶ ልደቱንም ሆነ የሌሎች ታሳሪዎችን ሰብዓዊ አያያዝ ለመከታተል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲገፋበት አበረታትተዋል።