መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 29፣2012-በሊባኖስ መዲና ቤሩት ባጋጠመው ከባድ ፍንዳታ የተነሳ ቢያንስ የ 78 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ 400 በላይ ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል

ለአደጋው መንስኤው ለስድስት ዓመታት ያለበቂ ጥንቃቄ ተከማችቶ የነበረ አሞኒየም ናይትሬት እንደነበረ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሚካኤል ኦሙን ተናግረዋል፡፡
በዛሬው እለት ካቢኔያቸውን የሚሰበስቡት ፕሬዝደንቱ የሁለት ሳምንት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚያሣልፍ ካቢኔው ይጠበቃል፡፡

ያጋጠመውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሀዘንን ሊባኖስ አሳልፋለች፡፡
የፕሬዝደንት ኦሙን አስተዳደር ለአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲውል መንግስታቸው የ 100 ቢሊዮን ሊሬ ፈንድ እንደሚለቅ ይፋ አድርገዋል፡፡

ያጋጠመውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ የሊባኖስ ቀይ መስቀል ዋና ሃላፊ ጆርጅ ኬታኒ ተጎጂዎች በተለያዩ አካባቢዎች አሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መነሻ ምን እንደሆነ በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡ በ 2013 ወደ አንድ መጋዘን እንዲከማች የተደረገ አሙኒየም ናይትሬት እንዳለ ግን ተነግሯል፡፡

በኢኮኖሚ እና በኮሮና ቀውስ ከባድ ችግር ውስጥ በነበረችው ሊባኖስ ያጋጠመው ፍንዳታ በሀገሪቱ ላይ መጥፎ ጥላን አሳድሯል፡፡

አሚኒየም ናይትሬት ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውል ሲሆን በዋናነት ለግብርና በማዳበሪያነትና ለፈንጅ መሳሪያ ይውላል፡፡ ይህ አሙኒየም ናይትሬት እሳት ከነካው ይበልጥ ተቀጣጣይ ስለመሆኑ መረጃዎች ያሣያሉ፡፡ በሚፈነዳበት ጊዜም በካይ የሆኑ ጋዞች እንደ ናይትሮጂን ኦክሳይድ እና አሙኒየም ጋዝ ሊለቀቅ ይችላል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *