
አሜሪካ በሙስና በመወንጀል እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናትን በገንዘብ ይደግፋል ስትል በእዉቁ የዙምባብዌ ባለሀብት ላይ ማዕቀብ ጥላለች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት እንዳስታወቀዉ የባለሀብቱ ኩዳክዋሺ ታግዊሪ ሀብት እና በአሜሪካ በሚገኙዉ የኩባንያዉ ንብረቶች እንዳይቀሳቀስ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡
ባለሀብቱ በርካታ የስራ ዉል ከመንግስት ባለስልጣናት ያለ ግልጽ ጨረታ የሚሰጠዉ ሲሆን በምላሹ ዉድ ተሸከርካሪዎችን ለመንግስት ባለስልጣናት እንደሚሰጥ ዋሽንግተን አስታዉቃለች፡፡ይህዉ ባለሀበት ከፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ጋር ቀረቤታ እንዳለዉ ተነግሯል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ