መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 7፣2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

የቬንዝዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ የቅርብ አማካሪ እና የኮሚኒኬሽን ሚንስትሩ ጆርግ ሮድሪጌዝ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ተሰማ፡፡

በህንድ በ24 ሰዓት ዉስጥ ብቻ 66,999 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛዉ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡2.4 ሚሊየን ህዝቦቿ በቫይረሱ በተጠቁባት ህንድ 47 ሺ ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

የናይጄሪያ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጂኦፍሪ ኦንየማ ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸዉ ተሰማ፡፡በሀገሪቱ በቫይረሱ 47,290 ሰዎች መጠቃታቸዉ ሲነገር 33,609 ሰዎች አገግመዋል፡፡ እስካሁን 956 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ከኮሮና ቫይረስ የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩ ተሰማ፡፡በአማካይ ከቫይረሱ የሚያገግሙ ሰዎች 75 በመቶ ሲሆን በመላዉ ዓለም 62 በመቶ ካለዉ የበለጠ ሆኗል፡፡

በሜክሲኮ ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ የ737 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡በሜክሲኮ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 498,380 ሲደርስ የ54,666 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በፔሩ በቀጣዩ እሁድ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ሊደረግ መሆኑ ተሰማ፡፡በየእለቱ ከ7ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተጠቁ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በመላዉ አለም በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 20,812,367 ሲደርስ የ747,327 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ 13,713,003 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *