መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 7፣2012-ሞዛምቢክ ቤሩት ውስጥ ለደረሰው ፍንዳታ ሀላፊነት አልወስድም ስትል አስታወቀች

ከቀናቶች በፊት በቤሩት ወደብ ተከማችቶ ፍንዳታ ባስከተለዉ አሙኒየም ናይትሬት መዳረሻዉ ሞዛምቢክ ነበረ መባሉን ተከትሎ የሞዛምቢክ መንግስት ሀላፊነቱን እንድወስድ የሚያስችል አይደለም ብለዋል፡፡የሞዛምቢክ ምክትል የፍትህ ሚንስትር የሆኑት ፊሊማኦ ሱአዚ ኬሚካሉ ወደ ሞዛምቢክ ሊመጣ እንደነበረ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡

ሆኖም ግን በሞዛምቢክ በዚሁ ዙርያ ተጠያቂ የሆነ አካል እንደሌለ አስታዉቀዋል፡፡በቤሩት የወደብ አስተዳዳሪ አካል ላይ ጣት መቀሰር ብቸኛ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከሞዛምቢክ ዓለም አቀፍ ባንክ ሰነድ አማካይነት በአንድ የሞዛምቢክ የማኒፋክቸር ኩባንያ እንዲመጣ የተደረገ ቢሆንም በገንዘብ እጥረት መድረስ አልቻለም፡፡ባልተከፈለ 100ሺ የአሜሪካን ዶላር የተነሳ ኬሚካሉ እንዲያዝ ሆኗል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *