መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 8፣2012-አሜሪካ በግል አውሮፕላን ወደ ኩባ የሚደረጉ የቻርተር በረራዎችን ከለከለች

የአሜሪካ አስተዳደር ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት ወደ ኩባ የሚያደርግ የቻርተር በረራዎችን የከለከለዉ በሀቫና መንግስት ላይ የኢኮኖሚ ጫና ለማሳደር ነዉ ተብሏል፡፡የዩናይትድ ስቴትስ የዉጪ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ ማይክ ፖምፕዮ የኩባ መንግስት ከቱሪዝም እና ጉዞ የሚያገኘዉን ገቢ የቪንዞዌላን መንግስትን ፈንድ ለማድረግ እየዋለ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በወርሃ ጥቅም የአሜሪካ መንግስት ከኮሚንስቷ ሀገር ኩባ መዲና ሀቫና ዉጪ ወደ ሌሎች ከተሞች በረራ እንዳይደረግ መከልከሉ ይታወሳል፡፡የኩባ ቱሪዝም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አስቀድሞ ክፍኛ ተጎድቷል፡፡

አሜሪካ የጣለችዉ ክልከላ ለህክምና እን ለረድኤት ተግባር የሚደረግ ጉዞን የሚከለክል አይደለም፡፡ከ50 ዓመታት ክልከላ በኃላ ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኩባ የሚደረግ በረራ በ2016 ዓመት መፈቀዱ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *