መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 11፤2012-በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መዛመት የተነሳ ኒውዚላንድ ሀገሪቱ ልታካሂደው የነበረውን ምርጫ ማዘዋወሯ ተሰማ

የኒውዚላንድ ጠ/ሚ የሆነችው አርደርን በዛሬው እለት እንዳስታወቀችው ሀገር አቀፏ የሀገሪቱ ምርጫ አስቀድሞ በሴፕቴምበር 19 ለማካሄድ ውጥን ተይዞ የነበረ ቢሆንም በአራት ሳምንት ተራዝሞ ኦክቶበር 17 እንዲደረግ መወሰኑን ይፋ አድርጋለች፡፡

በኒውዚላንድ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ በቫይረሱ የሚጠጉ ሰዎች ቁጥር መጨመር እና ከ 102 ቀናት ከቫይረሱ ኒውዚላድ ነፃ ከሆነች በኋላ በድጋሚ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች መገኘታቸው ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል፡፡

የኒውዚላንድ ዋንኛ የተቃዋሚ ቡድን ናሽናል ፓርቲ ምርጫው እንዲራዘም ጥሪ አድርጓል፡፡

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አልቻልንም ባሉ ፓርቲዎች ምርጫው ቢራዘምም ጠ/ሚኒስትሯ ግን ሁላችንም በተመሳሳይ ጀልባ ውስጥ መሆናችንን አትርሱ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *