መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 12፤2012 -በሱዳን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል

የሱዳን የሽግግር መንግስተት ከህዝብ የተሰጠውን አደራ በሚገባ መወጣት አልቻለም የሰብዓዊ መብት ረገጣ ተባብሷል ያሉ ዜጎች አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ ማሰማት ጀምረዋል፡፡የሱዳንን ሰንደቅ የያዙ ሰልፈኞች በመዲናዋ ካርቱም አደባባይ በመዉጣት የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ እንዲካሄድ በትላንትናዉ እለት ጠይቀዋል፡፡

ሀገሪቱን ለ30 ዓመታት የመሩት የኦማር አልበሽር አስተዳደር ከስልጣን እንዲወገድ ከፍተኛ ስራ የሰራዉ የሙያ ማህበራት ጥምረት በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ አስተዳደር የተነሳዉን ተቃዉሞ ተከትሎ የጸጥታ አካላት ከሚወስዱት የሀይል እርምጃ እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡

ሰልፈኞች የታገልነት ዓላማ ግቡን አልመታም እያሉ ሲሆን ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል፡፡የኦማር አልበሽር ከስልጣን መወገድን ተከትሎ በሲቪል እና በወታደሩ ጥምረት የሽግግር ምክር ቤት ቢመሰረትም ለዉጡ ቀርፋፋ ሆኗል የሚል ክስ በርትቷል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *