መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 12፤2012 -በአሜሪካ የዲሞክራቶች ጉባዔ ላይ ዶናልድ ትራምፕ ስህተት የሆኑ ፕሬዝዳንት ናቸዉ ሲሉ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ተናገሩ

የዲሞክራቶች የአራት ቀናት ስብሰባ መጀመሩንት ተከትሎ መልዕከት ያስተላለፉት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ ለአሜሪካ የማይሆኑ ፕሬዝዳንት ናቸዉ ከጊዜዉ ጋር የማይሄዱ ሰዉ ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ዩናይትድ ስቴትስን በድጋሚ ማደስ የሚችሉትን ጆ ባይደንን የአሜሪካ ህዝብ የግድ መምረጥ አለባቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሴናተሩ በርኒ ሳንደርስ በበኩላቸዉ ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንዲሆን እንፈልጋለን በአሜሪካ ዘመናዊ ታሪክ ይህ ምርጫ ወሳኝ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሳንደርስ እና ባይደን እንደ ዝቅተኛ የክፍያ መጠን፣የጤና ስርዓቱን በተመለከተ ልዩነቶች ያሏቸዉ ቢሆንም ሳንደርስ ልዩነታቸዉን ወደ ጎን ትተወ ለባይደን ድጋፍ ቸረዋል፡፡

የቀድሞ የኦሃዮ ገዢ እና የአመታት የሪፖብሊካኑ ሰዉ ጆን ካሲች ትራምፕ አሜሪካዉያኑን ከፋፍሏል፡፡ለዩናይትድ ስቴትስ አንድነት ሪፓብሊካዉያኑ ባይደንን ሊመርጡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኒዉዮርክ ግዛት ገዢ አንድሪዉ ኩሞ በበኩላቸዉ ትራምፕን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በማነጻፀር ተችተዋል፡፡ቫይረሱ የሰዉ ልጅን ሲያጠቃ ሰዉነት ይዳከማል እራሱን መከላከል ያቅተዋል ባለፉት ጥቂት ዓመታት የአሜሪካ ፖለቲካ እንዲህ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ጠንካራ ሰዉ ቫይረሱን እንደሚዋጋ ሁሉ የአሜሪካ መከፋፈልንም እንደዛዉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *