መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 14፣2012-የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ አን ተጨማሪ ሀላፊነቶችን ለእህታቸው መስጠታቸዉ ተሰማ

የሰሜን ኮርያዉ መሪ ኪም ጆንግ አን ለእህታቸዉ እና በቅርባቸዉ ለሚገኙ የስራ አጋሮቻቸዉ ተጨማሪ የስራ ሀላፊነት መስጠታቸዉ ተሰምቷል፡፡የደቡብ ኮርያ የስለላ ኤጀንሲ እንዳስታወቀዉ ኪም ያለባቸዉን የስራ ጫና ለማቃለል በሚል ለእህታቸዉ ዮ ጆንግ የስራ ድርሻን አጋርተዋል፡፡

ኪም ጆንግ አን አሁንም የሰሜን ኮርያ ባለሙሉ ስልጣን መሪ ቢሆኑም አንዳንድ ሀላፊነቶች ግን ከእጃቸዉ እየወጣ ይገኛል፡፡ሰሜን ኮርያን በሚመለከት ከአሜሪካ ጋር እና ደቡብ ኮርያ ጋር ለሚደረግ ዉይይት ድርሻ በመዉሰድ የምትመራዉ ዮ ጆንግ ትሆናለች፡፡

በአራት ዓመት ከኪም ጆንግ አን የምታንሰዉ ዮ ጆንግ በስዊዘርላንድ በርን ከታላቅ ወንድሟ ጋር ትምህርቷን ተከታትላለች፡፡ከኪም ቤተሰብ እ.ኤ.አ በ2018 ደቡብ ኮርያን በመጎብኘቷ ዓለም አቀፉ ትኩረትን እንድታገኝ አድርጓት እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *